Stay updated with the latest news and
developments from our community.
"ግፋታ የዘመን መቁጠሪያ ብቻ ሳይሆን የታሪክ የመንፈሳዊ ማህበራዊ እሴትና የአንድነት መገለጫ እንዲሁም የእርቅ የመከባበር የሰላምና የአዲስ ተስፋ መጀመሪያ ነው" - ክቡራን አምባሳደር አብርሃም መንግስቱ በዋሽንግተን ዲሲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ዲፕሎማቲክ ሚሽን ዋና ኃላፊ አምባሳደር
ወላይታ ግሎባልስ አሊያንስ (WoGA) ግፋታ በዩኔስኮ አለም አቀፍ የማይዳሰስ ቅርስነት መመዝገብ በተመለከተ ያዘጋጀው ህዝባዊ የሚሳምና ኬክ ቆረሳ ፕሮግራም የተከበሩ አምባሳደር አብርሃም መንግስቱ በዩናይትድ ስቴትስ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ዲፕሎማቲክ ሚሽን ኃላፊና ሌሎች የአገር ውስጥና ውጭ ሀገር እንግዶች በተገኙበት ጃንዋሪ 11/2026 በድምቀትና በተሳካ ሁኔታ ተከብሯል::
በዩኔስኮ የአለም የሰው ልጆች ቅርስ ተደርጎ ጥበቃና ክብካቤ እንዲደረግለት የተመዘገበው የወላይታ ዘመን መለወጫ በዓል ማለትም ግፋታ የዓለም ፖለቲካና ኢኮኖሚ ማዕከል በሆነው ዩናይት ስቴትስ ዋና ከተማ ዋሽንግተን ዲሲ ቨርጂኒያና ሜሪላንድ አካባቢ በሚኖሩ ተወላጆችና ወዳጆች በወላይታ ግሎባል አሊያንስ WoGA አስተባባሪነት ዛሬ በድምቀት ተከብሯል::
በዝግጅቱ ላይ ክቡር አምባሳደር አብርሃም መንግስቱ በዩናይትድ ስቴትስ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ዲፕሎማቲክ ሚሽን ዋና ሀላፊና የክብር አምባሳደር ብናልፍ ዓንዱዓለም ተወካይ ክቡር አቶ ጥበቡ ታፈሰ የኤምባስው ዳያፖራ ጉዳይ ሀላፊና ሌሎች ዲፕሎማቶች የተካተቱበት ቡድን "ከንግዲህ ግፋታ እሴትነቱ የወላይታ ብቻ ሳይሆን የመላዉ ኢትዮጵያውያን ደማቅ በዓል በመሆኑ እንኮራበታለን በጋራ እናከባከባለን እንደምቅበታለን" የሚል መልእክት አስተላልፈዋል ::
የኢትዮጵያ ኮምዩኒቲ ዴቬሎፕመንት ካውንስል (ECDC) በመወከል የተገኙት አቶ አክሊሉ የ ECDC ዋና ዳይሬክተር ከተከበሩ ዶክተር ጸሃይ ተፈራ የተላከ የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት ለወላይታ ግሎባል አሊያንስ በዩናይትድ ስቴትስ ለሚገኙ ወላይታ ኮሚኒቲ አባላትና እንዲሁም ለጠቅላላው የወላይታና ኢትዮጵያ ህዝብ አስተላልፈዋል ::
በክብር እንግድነት ተጋብዘው ዝግጅቱን የታደሙት የጆርጅታውን ዩንቨርስቲ የአፍሪካ ጥናት ፕሮግራም እንዲሁም የሆዋርድ ዩኒቨርሲቲ ስኩል ኦፍ ሶሻል ወርክ ፕሮፌሰሮች የሆኑ አሜሪካኖች "በዓሉ የአለም ቅርስ በመሆኑ እኛንም ይመለከተናልና የስነ ስርዓቱ አካል አድርጋችሁ ስለጋብዛችሁን ወላይታ ግሎባል አሊያንስ (WoGA) እናመሰግናለን የወላይታ ኮሚኒቲውም እንኳን ደስ ያላችሁ" የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል ::
ሌሎች የዚህ ዝግጅት ግርማ ሞገስ የነበሩት ወላይታና ጠቅላላ ኢትዮጵያን እድሜያቸውን ሙሉ በብቃት ከግማሽ ክፍለ ዘመን በላይ አገልግለው ጡረታ ላይ ከሚገኙ ጥሪ ከተደረገላቸው ተጋባዥ አንጋፋና ስመ ጥር የሀገር ሽማግሌዎች መካከል
👉 የተከበሩ አቶ ጴጥሮስ ገበቶ
👉 የተከበሩ አቶ ዳዊት ሽምብሎ
👉 የተከበሩ አቶ መንገሻ ግዛው
በየበኩላቸው ጊዜ ወስደው ከእንኳን ደስ አለን መልዕክት በተጨማሪ እጅግ ልብ የሚያሞቅ አባታዊ ምከር ለግሰዋል::
በጠቅላላ አራት ሰዓት የዘለቀው ይህ ያዳራሽ ውስጥ ስነ ስርዓት ከምሳ ግብዣ በኋላ የኢትዮጵያ ኮምዩኒቲ ድቨሎፕመንት ካውንስል ተወካይ አማካኝነት የግፋታ ኬክ ተቆርሶ የታዳሚዎች አስተያየት ከተደመጠና ለዝግጅቱ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱት ግለሰቦች WoGA ያዘጋጀላቸው የምስክር ወረቀት ከተከበሩ አቶ ጴጥሮስ ገበቱ እጅ ተቀብለው የመዝጊያ ንግግር በግሎባል አሊያንስ አመራሮች ከተደረገ በኋላ 5:00 pm ዝግጅቱ በደማቅ ስኬት ተጠናቋል::
ይህ ከወላይታ ውጪ ሌላው ኢትዮጵያዊና አሜሪካዊው ጭምር ግፋታ የአለም ቅርስ ሆኖ የተመዘገበው የኔም በዓል ነው በማለት ደስታውን ለመግለጽ ጊዜ መስዋዕት አድርገው የተሳተፈበት ዝግጅት የተሳካው ያለ ተግዳሮት አልነበረም:: በራሳቸው የተሸነፉ ህዝባዊ ዓላማ የሌላቸው ማህበረሰብ ማከፋፈል የህይወታቸው ግብ አድርገው የሚንቀሳቀሱ ርካሽ ግለሰቦች " የወላይታን በዓል ለማክበር እንግዶችን ጋብዘን አዳራሽ ተከራይተን የተጋበዙ እንግዶች ሲመጡ አዳራሽ ሰው ተሰብስበው ፕሮግራሙን እንዳይደምቅ ተጋብዘው በሚመጡ እንግዶች ፊት ወላይታን አሳንሶ ለማሳየት ቤት ለቤት እየዞሩና ስልክ እየደወሉ ለሁለት ሳምንት አፍራሽ ቅስቀሳ እያካሄዱ ቆይተው አልተሳካላቸው:: ግባቸውና ህልማቸው ወላይታን አሳንሶ ማሳየት የወላይታ ህዝብ ጥቅም እና ክብር ሽጠው ቅንጭብጫዊ የግል ጥቅም ማሳደድ ነበር:: የግል ስምና ጥቅም አሳዳጆች በወላይታ ህዝብ ክብርና ጥቅም ላይ የመነገድ እድል እስከሚመናመን ወላይታ ግሎባል አሊያንስ እንቅልፍ አይኖረው:: በዚህ ጉዳይ ዙሪያ ወላይታ ግሎባል አሊያንስ ሌላ ዝርዝር መግለጫ በቅርብ ቀን የሚያቀርብበት ይሆናል ::
ለማጠቃለል: ለዚህ ስኬት የተጋችሁ ሁሉ ክብር ይገባችሐል:: እንዲሁም ለህዝባችን ክብርና ጥቅም የወላይታ ግሎባል አሊያንስ ለሚያደርገው ጥረት ሙሉ እውቅና ሰጥታችሁ ለወደፊትም ትብብራችሁ እንደሚቀጥል ቃል የገባችሁልን በአሜሪካ የኢፌድሪ ኤምባሲ ባለሙሉ ስልጠና አምባሳደር : የዲፕሎማቲክ ሚሽን ዋና ሀላፊ አምባሳደር : የዳያስራ ጉዳይ ዋና ኃላፊ : የኢትዮጵያ ኮምኒቲ ዲቨሎፕመንት ካውንስል በዩናይትድ ስቴትስ (ECDC) እና በመካከላችን የተገኛችሁ ጌጦቻችንና ለዘመናት የካበቴ እውቀትና ልምድ ቋት የሆናችሁ አንጋፋ አባቶቻችን እንዲሁም በጠቅላላው ጥሪያችን አክብራችሁ ለዝግጅቱ ድምቀትና ስኬት የሆናችሁልን በሙሉ ወላይታ ግሎባል አሊያንስ ልባዊ ምስጋና ያቀርባል ::
ሁላችሁም ለዚህ ታሪካዊ ክስተት እንኳን አደረሳችሁ!
