WoGA ባካሄደው ዳሰሳ ጥናት ህዝብ የሚጎዱ አካላትና ተግባራት በመለየት ለትግሉ ለሕግ ባለሙያዎች የአጋርነት ጥሪ አቀረበ::

  • Category :Community
  • Date :15th Sep 2025
  • Time :5 Min Read
Community 15th Sep 2025

WoGA ባካሄደው ዳሰሳ ጥናት ህዝብ የሚጎዱ አካላትና ተግባራት በመለየት ለትግሉ ለሕግ ባለሙያዎች የአጋርነት ጥሪ አቀረበ::

Stay updated with the latest news and developments from our community.

WoGA ባካሄደው ዳሰሳ ጥናት ህዝብ የሚጎዱ አካላትና ተግባራት በመለየት ለትግሉ ለሕግ ባለሙያዎች የአጋርነት ጥሪ አቀረበ የወላይታ አለም አቀፍ ጥምረት ወይም በእንግሊዘኛው Wolayta Global Alliance (WoGA) ለድርጊት መርሐ ግብር ይረዳው ዘንድ ባካሄደው አጭር የዳሰሳ ጥናት የአካባቢው ህዝብ መብት ክብርና ጥቅም በሚጎዳ ተግባር ላይ ተሳታፊ የሆኑ አራት ዋና ዋና አካላት ልይታ ያደረገ ሲሆን እነዚህን አካላት አፍራሽ ሚና ለመከላከል የጠቅላላው ማህበረሰብ እና በተለይም የኤሊቶች ሁሉ አቀፍ የጋራ ጥረት እንደሚጠይቅ አስምሮበታል:: ጥምረቱ (WoGA) ለሕግ ባለሙያዎች በተለይም ለዳኞችና ጠበቆች አስቸኳይ የትግል አጋርነት ጥሪ አስተላልፏል:: በጥሪው ጥምረቱ NGOዎችና ሲቪክ ማህበራት የአንድ ማህበረሰብ የጋራ መብት አለኝታና መከታዎች መሆናቸውን አመልክቷል :: የወላይታ ዓለም አቀፍ ጥምረት (WoGA) ከሀገር ዉጭ ያሉት ተወላጆች እርስ በርስ እንዲደጋገፉ ከማያያዝ ጎን ለጎን ሀገር ቤት ያለው ደሃው ድምጽ-አልባ ህዝብ መብት ጥቅምና ክብሩን ለማስጠበቅ ከፍተኛ ተኩረት ሰጥቶ በቁርጠኝነት እንደሚንቀሳቀስ ገልፀዋል :: WoGA ባካሄደው አጭር ዳሰሳ አሁን ባለው ሁኔታ የወላይታ ህዝብ መብት ክብርና ጥቅም የሚጎዱ ተግባራት ላይ በዋናነት አሉታዊ ተሳታፊ የሆኑ አራት አካላት የለያቸው ሲሆን እነዚህም 1) የመንግስት ተሿሚዎች :- ሀላፊነታቸውን የዘነጉና የግል ጥቅም አሳዳጅ ተሿሚዎች ስልጣን ያለ አግባብ ተጠቅመው የህዝብ ሃብት ( ለምሳሌ መሬት) ይወርራሉ: ጉቦ ይቀበላሉ: ውክልናቸውን ሽጠው አለቆቻቸውን ለማስደሰት ኢ-ህዝባዊ የሆኑ ውሳኔዎች ተቀብለው የህዝቡን ጥቅም አሳልፈው በመስጠት ወስኔውን ያስፈጽማሉ:: 2) በህዝብ ህመምና ጉስቁልና የሚነግዱ መሰሪና ጨካኝ ባለሀብቶች:- እነዚህ ለታይታ በየገቢ ማሰባሰቢያ መድረክ ልማታዊና ለጋሽ መስለው የተወሰነ ገንዘብ ቃል በመግባት በተጨባጭ ግን ብዙ መቶ ሚሊዮን ብር የሚያወጣ የህዝብ መሬት ከተሿሚዎች ጋር ተሻርከው ይዘርፋሉ:: 3) የአካባቢው ደላላዎች :- እነዚህ ተራ ቁጥር 1 ስር ለተጠቀሱት ተሿሚዎችና ስስ ቦታ የተመደቡ ባለሙያዎች ጋር ኔትወርክ በመፍጠር የከተማ መሬት የመሳሰሉት የህዝብ ሀብት ሽጠው የተጣራ ጥቅም ያቃበሏቸዋል:: 4) ስግብግብ ዲያስፖራዎች:- የእነዚህ የዝርፊያ አካሄድ ተራ ቁጥር 2 ስር እንደተጠቀሱት መሰሪ ባለሀብቶች ጋር ተመሳሳይ ሲሆን ወሳኝ የሆኑ ገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅቶች (ኤቨንትስ) ወቅት ብቻ እየጠበቁ ብቅ በማለት በአደባባይ ግንባታቸውን እያስመቱ ከተሿሚ ካድሬዎች ጋር ተሻርከው ኮንዶሚኒየም ቤቶች: የከተማ ቦታዎች እና የገጠር ኢንቨስትመንት መሬት እየቀፈሉ ያለልማት ለመክበር ይንደፋደፋሉ: ማገዝ የሚገባቸውን ድሃ ማህበረሰብ ያለእፍረት መልሰው በጭካኔ የዘርፉታል:: ስለዚህ እነዚህን አካላት ለማጋለጥና ለመታገል ብሎም የህዝብ ክብር መብትና ጥቅም ከእነሱ ጥምር ወረራ ለመከላከል Wolayta Global Alliance (WoGA) በአካባቢው ከሚገኙ የህዝብ ክብር ተቆርቋሪ ከሆኑት የህግ ባለሙያዎች ( ጠበቆችና ዳኞች) ጋር ጠንካራ ሙያዊ አጋርነት ለመፍጠር እንደሚፈልግ አብራርቷል:: ስለዚህ WoGA በመግለጫው ወላይታ አካባቢ የሚገኙ የሕግ ባለሙያዎች በተለይ ጠበቆችና ዳኞች የጥምረቱን ዌብሳይት (www.wogalliance.org) በመጎብኘት በተቀመጠው የ WoGA አድራሻ አማእል, Facebook, Telegram, ወይም WhatsApp በሚመቻቸው በመጠቀም የትምህርቱን አስተባባሪዎች እንዲያገኙና የዝብ መብት ክብርና ጥቅም ለማስመለስ ለሚደረግ ጥረት ሁኔታ አጋር በመሆን ህዝባዊና ሙያው ሀላፊነታቸውን በጋራ እንዲወጡ ጥሪውን አቅርቧል :: የህዝብ መብት ክብርና ጥቅም ማስከበር የተባበረ ብርቱ ጥረት ይጠይቃል !!! Wolayta Global Alliance (WoGA) ኦክቶቨር 1, 2025, Washington DC, USA
Share this article:

Recent News

ወላይታ ድቻ ለኮፌዴሬሽን የመጀመርያ ዙር ማጣሪያ አል ኢትሃድን ዓርብ ይገጥማል::

1st Oct 2025

Related News

Discover more stories and updates from our community.

Community
1st Oct 2025

ወላይታ ድቻ ለኮፌዴሬሽን የመጀመርያ ዙር ማጣሪያ አል ኢትሃድን ዓርብ ይገጥማል::

Read More

Subscribe to Newsletter!

Subscribe to get latest updates and information.