Stay updated with the latest news and
developments from our community.
አበላ አባያ ህዝብ እየተበደለና እየተገደለ ለዘለዓለም አይቀጥልም፤ አስተማማኝ ጥበቃ የማይደረግለት ከሆነ ህዝብ ራስን የመከላከል መብት ሊከበርለት ይገባል፡፡ ድርጅታችን Wolayta Global Alliance-WoGA (ዎጋ) ለትርፍ ያልቆመ መንግስታዊ ያልሆነ የዎላይታ ተወላጆችና ወዳጆች ዓለም አቀፍ ጥምረት ሲሆን የህዝብ ክብር ማህበራዊ ልማት ፍትህና ሰብአዊ መብት ለማረጋገጥ ለሚደርገው ሁለንተናዊ ኢንቅስቃሴ በቁርጠኝነት እያገዘ የሚገኝ በአሜሪካ ህግ ተመዝግቦ መቀመጫውን ዋሽንግተን ዲሲ አድርጎ የሚሰራ ጥምረት ነው፡፡ የድርጅታችን ቦርድ ኖቨምብር 14/2025 ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ ሰሞኑን በዎላይታና ሲዳማ ወሰን አበላ አባያ ከወላይታ ወገን ውድ ህይወታቸው ለተቀጠፈ ሁለት የፖሊስ አባላት ልባዊ ሀዘኑን እየገለጸ ቀጥሎ ያለውን መግለጫ ያቀርባል፡፡
ይህ በአክባቢ በተለምዶ 8ቱ የብላቴ መንደሮች ተብሎ በሚታወቀው ወሰን ዙሪያ ያልተቋጨ የወሰን ውዝግብ መነሻነት በየጊዜው ከሲዳማ በኩል ወሰን አቋረጠው ጥቃት በሚሰነዝሩ ነፍስ በላዎች ቁጥሩ ቀላለ ያልሆነ ንጹሃን ነዋሪና አልፎ አልፎም በሥራ ስምሪት ላይ የሚገኙ ፖሊሶች ሰለባ እየሆኑ ደማቸው ደመከልብ ሆኖ ቀርቷል፡፡ ከሶስት ሳምንት በፊት የዎጋ ምንጮች ባደረጉት ማጣራት አከባቢው ላይ አዲስ ጥቃት እያንዣበበ መሆኑንና ክሲዳማ የተነሱት መሬት ወራሪዎች በስምንቱ መንደር ክመወሰን ተሻግረው ወደ ዎላይታ ዘልቀው በመገባት በልማት ማህበሩ (ዎልማ) ስም ተመዝግቦ የሚገኝ ይዞታ ላይ ጭምር ቤት ሰርተው እየሰፈሩ መሆኑ እየታየ የዞኑ መስተዳድር በታጣቂ የተደገፈ መሬት ወረራ ለማስቆም እርምጃ አለመውሰዱንና የወላይታ ዞን አመራር የተሳተፉበት የወሰን አክባቢ ጸጥታ ምክክር ሀዋሳ መካሄድ ተከትሎ ወዲያው የሚሰሩት ቤቶች ቁጥራቸው እየጨመረ መምጣቱን ነዋሪዎቹ በስጋት ለዎጋ ገልጸው ነበር፡፡ ከሲዳማ በኩል በክልሉ ታጣቂ ሽፋን ከሚያገኙ ግለሰብ መሬት ወራሪዎች በተጨማሪ የክልሉ ክፍተኛ የፖለቲካ ፓሪቲ ሀላፊውና ቤተሰቦቹ ሁሉ እጃቸው እንዳለበት የዎላይታ አርሶአደሮች በማወሳት ሁሌ ከዞኑ ትኩረትና ጥበቃ እየፈለጉ እንደተነፈጋቸውና በቤታቸው ራስ መጠበቂያ ደህና ቆጥ እንኳን እንዳይይዙ በየጊዜው ተከታትለው የዞኑ አመራር ትጥቅ እያስፈታ ባዶ እጅ አስቀርተው ከአጎራባች መዋቅር ለሚነሱ ሲዳማ ታጣቂዎች ጥቃት ሰለባ እንዳደረጓቸው የአከባቢው ነዋሪ ህዝብ ያማርራሉ፡፡ ከቅድመ አያቶቻቸው ዘመን አንስተው አበላ አባያ አክባቢ ነዋሪ የሆኑ የዎጋ ምንጮች በሚያቀርቡት መረጃ የዎላይታ ህዝብ ከሲዳማ ጋር ያለው ታሪካዊ ወሰን ዎራንቻ ማጧ የሚባል ቦታ እንደሆነና ከዚያ ውጭ ከሁለቱም ወገን የሚወጡ ሹማምንት የግል ሥልጣን ለማደላደል ወይም ጎሳዊና ቤተሰባዊ ፕሮጀክት ለማስፋፋት በሚያደረጉት ስውር አካሄድ ሁለቱን አጎራባች ህዝብ ለከፋ ግጭት እያጋለጡት መሆኑን አጥብቀው ያወግዙታል፡፡ ዎጋ በምንጮቹ በኩል ከአክባቢው ባሰባሰበው መረጃ መሰረት የአባያ ይዞታና ህዝብ ደህንነት ከማስጠበቅ አንጻር ህዝቡ በዎላይታ ዞን አስተዳደር ሆነ በደቡብ ክልል ፍትህና ጸጥታ ዘርፍ እንዲሁም ዎላታን በፌዴራል በሚወክሉት ሽማምንት ላይ እምነቱ ተሟጥጧል፡፡ የራሱን ወረዳ መዋቅር የሚጠይቅ ሰላማዊ የዘይሴ ህዝብ በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ትዕዛዝ እየተነሳ የሚጨፈጭፍ የደቡብ ክልል ልዩ ሐይል አበላ አባያ በየጊዜው ከሲዳማ ክልል በሚነሱ ታጣቂዎች ህዝብ ሲጨፈጭም አይከላከልም የዎላይታ ሹማምንትም በዝምታ ይተባበራቸዋል በማለት ህዝቡ ያማርራል፡፡
የወላይታ ተወላጆችና ወዳጆች ዓለም አቀፍ ጥመረት ዎጋ የዜጎች በህይወት የመኖርና ሰላማቸው ተጠብቆ ወጥቶ የመገባት ህገ መንግስታዊ መብት ከመንግስት ዋስትና ማግኘት እንዳለበት አጥብቆ ያምናል፡፡ የማህበረሰብ ዘላቂ ልማት መሰረቱ የተረጋጋ ሰላም እንደሆነ አጽናኦት ይሰጣል፡፤ ስለዚህ የዞኑ መንግሥት ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልልና ከፌዴራል መንግሥት አግባብነት ካላቸው ክፍሎች ጋር የአበላ አባያ አክባቢ ደም መፋሰስ አንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ማስቆም የሚቻልበት አቅጣጫ መከተል ሀላፊነት አለበት፡፡ የመንግሥት ቁጥር አንድ ሀላፊነት የዜጎች ህይወትና ንብረት ደህነት መጠበቅ በመሆኑ፦
1. የዎላይታ ዞን መስተዳድር በሐላፊነት ስሜት ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልልና ፌዴራል መንግሥት ጋር በመሆን ለአበላ አባያ ወገኖች አስተማማኝ ሰላምና ጸጥታ አስከባሪ ሐይል እንዲያሰማራ፤ ለተገደሉት ወገኖች ቤተሰብ በቂ ካሳ እነዲክፍልና ለተድጋጋሚ ደም መፈሰስና ሌላ የባሰ ህዝብ ለህዝብ ግጭት ሊያስነሳ የሚችል ሳይቋጭ የተንጠለጠለ የወሰን ውዝግብ ፍትሓዊና ዘላቂ ውሳኔ እንዲያገኝ ያለመታከት መሥራት የዞኑ ሐላፊነት መሆኑን የዞኑ መዋቅር ተረድቶ በትኩረት እንዲንቀሳቀስ
2. ህዝብ ለደህንነትና ለሰላም ዋስትናው መንግሥት ላይ ከሚያደርገው ተስፋ ጎን ለጎን የራስን ሰላም በራሱ ለመክላከል እንዲያግዘው በህጋዊ መንገድ በማስመዝገብ በግሉ የመታጠቅ አማራጭ ተፈጠሮአዊ ስለሚሆን የዎላይታ ዞን ካቢኔ ይህን አስወስኖ በአስቸኳይ የአክባቢው ህዝብ በህጋዊ መንገድ በግሉ እንዲታጠቅ እንዲፈቅድ እንጠይቃለን፡፡
3. የሰሞኑን ጨምሮ ለተሰውት ውድ የህዝብ ልጆች ቤተሰብ የሚደረግ ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥልና ዎላይታ ግሎባል አሊያንስ (ዎጋ) በዚህ ረገድ የድርሻውን ለመወጣት ዝግጁነቱን እናረጋግጣለን፡፡ ክቡር ህይወታቸው ለተሰዋው ብርቅዬ ወጣቶች በድጋሚ ሀዘናን እየገለጸን ለነፍሳቸው ዘላለማዊ እረፍትን ለቤተስብና መላው የዎላይታ ህዝብ ደግሞ መጽናናትን እንመኛለን፡፡
ዎጋ ለህዝብ ክብር መብትና ጥቅም ይተጋል!
ዎላይታ ግሎባል አሊያንስ (WoGA) ሥራ አመራር ቦርድ
